የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በ2016 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ዛሬ የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር አከናውኗል፡፡
ሽልማቱ በአይነትና በገንዘብ የተበረከተ ሲሆን፤ በበጀት አመቱ አገልግሎት አሰጣጥ ውጤት መሻሻል የሰራተኛው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበረ ተጠቁሟል።
በበጀት አመቱም ቂርቆስ፣ አቃቂ ቃሊቲና ልደታ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በቅደም ተከተል ተሸላሚ ሆነዋል።
በእለቱ እውቅና የተሰጣቸው ሰራተኞችና የባለድርሻ አካላት ተቋማት በተሰጣቸው እውቅናና ሽልማት ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፤ ሽልማቱ የበለጠ መነሳሳትን በመፍጠር በቀጣይ ስራቸው ይበልጥ እንዲሰሩ እንደሚያተጋቸውም ጭምር ገልጸዋል፡፡
በእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብሩም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክንፈ አዲስ፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስና የቢሮው አመራሮች፣ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደሳለኝና አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው የባለስልጣኑ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።